ትራምፕ በተገኙበት የዋይት ሐውስ ጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ሲከፈት የተፈጠረውን ትርምስ የሚያሳይ ምስል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች የእራት ግብዣ ላይ የተገኙ እንግዶች ጠረጴዛ እና ወንበሮች ስር ተደብቀዋልየንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት የዋይት ሐውስ ጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ሲከፈት እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በፍጥነት አካባቢውን እንዲለቅቁ ተደርጓል።
የእራት ግብዣው ተዘጋጅቶ የነበረው በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የሒልተን ሆቴል ነው።
አንዳንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ስም እና ዝና ያላቸው ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች በዋሺንግተን ሒልተን አዳራሽ ውስጥ ተገኝተው ነበር።
ተኩሱ እንደተሰማ ከጠረጴዛ እና ወንበሮች ስር ለመደበቅ ተገድደዋል።
ተጠርጣሪው ነዋሪነቱን በካሊፎርኒያ ያደረገው የ31 ዓመቱ ኮል ቶማስ አለን መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንደሚመሠረትበት ተገልጿል።
አንድ የአሜሪካ የደህንነት እና ጸጥታ ባልደረባ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ሕክምና እንደተደረገለት የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
በምሽቱ የተፈጠረው በምስል ምን ይመስላል?

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የምስሉ መግለጫ, የደህንነት እና ጸጥታ አባላት ትራምፕ ከመድረኩ ላይ በፍጥነት እንዲወርዱ ሲያደርጉ ሌሎች ወታደሮች ደግሞ አካባቢው ላይ ቅኝት አድርገዋል
የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, የጤና ሚኒስትሩ ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ከአዳራሹ እንዲወጡ ሲደረግ
የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ከትራምፕ የቅርብ ረዳቶች መካከል አንዱ የሆኑት ስቴፈን ሚለር እና ባለቤታቸው ካቲ ደህንነቱ ወደተጠበቀበት ስፍራ ተወስደዋል
የፎቶው ባለመብት, Reuters
የምስሉ መግለጫ, የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን በደህንነት አባላት ከአዳራሹ እንዲወጡ ተደርጓል
የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, @realDonaldTrump/ Truth Social
የምስሉ መግለጫ, በትራምፕ ትዕዛዝ ዋይት ሐውስ ያጋራው ምሰል ላይ ከላይ ምንም ዓይነት ልብስ ያልለበሰ ሰው እጆቹ የኋሊት ታስረው መሬት ላይ ተኝቶ ይታያል። ከጀርባው የደህንነት አባላት ቆመው ይታያሉ
የፎቶው ባለመብት, Reuters
የምስሉ መግለጫ, ተኩስ በተከፈተበት ዋሺንግተን ሒልተን ሆቴል የፖሊስ መኪና ቆሞ ይታያል
የፎቶው ባለመብት, Anadolu via Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ የተጠርጣሪውን ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ካጋሩ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣ በዋይት ሐውስ ጋዜጣዊ መስጫ ክፍል ውስጥ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቆወች ምላሽ ሰጥተዋል
የፎቶው ባለመብት, AFP via Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በርካቶቹ የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች በግብዣው ላይ ለመገኘት ያደረጉትን እራት ልብስ እና ሱፍ እንደለበሱ የትራምፕን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝተዋል
የፎቶው ባለመብት, Bloomberg via Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ሜላኒያ ትራምፕ ከካሮላይን ሌይቪት፣ ፒት ሄግሴት፣ ማርኮ ሩቢዮ እና ሌሎች ባለሥልታነት አጠገብ ቆማ ትታያለች። ትራምፕ ለባለቤታቸው ሜላኒያ የሒልተን ሆቴሉ ክስተት "አሰቃቂ" እንደነበር ተናግረዋል
የፎቶው ባለመብት, EPA
የምስሉ መግለጫ, እንግዶች አዳራሹን ለቅቀው ከወጡ በኋላ የእራት ግብዣው ይቀጥላል ተብሎ የነበረ በመሆኑ ግራ በመጋባት ደጅ ቆመው ታይተዋል