
የፎቶው ባለመብት, Reuters
ኢራን ረቡዕ ዕለት በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ኮንቴይነር በጫኑ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተገለፀ።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ
አባላት ረቡዕ ጠዋት ሦስት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የተኩስ
አቁሙን ላልተወሰነ ጊዜ ካራዘሙ በኋላ የደረሰ ነው።
የብሪታኒያ ጦር አካል የሆነው የዩኬ ባሕር ትራንስፖርት ማዕከል ሦስት መርከቦች
ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጾ አንደኛው ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የባህር ትራንስፖርት ማዕከል የመጀመርያው
መርከብ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ ጥቂት ሰዓታት በኋላ ሁለት መርከቦች ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ገልጿል።
እስካሁን ድረስ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አልተሰማም።
ጥቃት የተፈጸመባቸው ሁለት መርከቦች በግሪክ እና ዩኤኢ ባለቤትነት የተያዙ መሆናቸው ተገልጿል።
የባህር ትራንስፖርት ላይ ክትትል የሚያደርገው ማዕከል በሁለቱ መርከቦች ላይ ጥቃት የፈጸመው ማን እንደሆነ ወዲያውኑ አለመታወቁን ገልጿል።
ነገር ግን የመጀመርያው መርከብ ላይ ጥቃት የፈጸሙት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጀልባዎች ሁለቱ መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የሚል ግምት አለ።
የኢራን መንግሥት ጠንካራ ደጋፊዎች የተኩስ አቁሙ ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት በመላ አገሪቱ ሚሳዔሎችን እና ማስወንጨፊያዎችን በአደባባይ በማሳየት ሠልፎችን አካሂደዋል።
አሜሪካ እና እስራኤል የሚፈጽሙትን የአየር ድብደባ ካቆሙ በኋላ ኢራን ወደ እስራኤል
እና የባሕረ ሰላጤው አገራት የምትተኩሳቸውን ድሮኖች እና ሚሳዔሎች አቁማለች።
ረቡዕ ዕለት በወሽመጡ ላይ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እና ቀደም ሲል አሜሪካ የኢራን መርከቦችን መከልከሏ ስጋቱ አሁንም በወሽመጡ ላይ መቀጠሉን ያሳያል።
ትራምፕ አሜሪካ የኢራንን ወደቦች መዝጋት እንደምትቀጥል የተናገሩ ሲሆን ኢራን ደግሞ እርምጃው “ተቀባይነት እንደሌለው” በመግለጽ
በኢዝላማባድ በሚደረገውውይይት ላይ ሳትሳተፍ ቀርታለች።
የአብዮታዊ ጥበቃ ዘብ ረቡዕ ዕለት
“በቀጣናው ውስጥ በሚገኙ ንብረቶቹ ላይ ከጠላት አስተሳሰብ በላይ ከባድ የሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም” ዝቷል።