ትራምፕ በተገኙበት የዋይት ሐውስ ጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ሲከፈት የተፈጠረውን ትርምስ የሚያሳይ ምስል

የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት የዋይት ሐውስ ጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ሲከፈት እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በፍጥነት አካባቢውን እንዲለቅቁ ተደርጓል።

የእራት ግብዣው ተዘጋጅቶ የነበረው በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የሒልተን ሆቴል ነው።

አንዳንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ስም እና ዝና ያላቸው ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች በዋሺንግተን ሒልተን አዳራሽ ውስጥ ተገኝተው ነበር።

ተኩሱ እንደተሰማ ከጠረጴዛ እና ወንበሮች ስር ለመደበቅ ተገድደዋል።

ተጠርጣሪው ነዋሪነቱን በካሊፎርኒያ ያደረገው የ31 ዓመቱ ኮል ቶማስ አለን መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንደሚመሠረትበት ተገልጿል።

አንድ የአሜሪካ የደህንነት እና ጸጥታ ባልደረባ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ሕክምና እንደተደረገለት የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በምሽቱ የተፈጠረው በምስል ምን ይመስላል?