ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ "ዲያቢሎስን ሦስት ጊዜ እንደተመለከቱ" በግል ማስታወሻቸው ሰፍሮ ተገኘ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ
የምስሉ መግለጫ, የቀድሞው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የቀድሞው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሕይወት ዘመናቸው ዲያቢሎስን ሦስት ጊዜ እንዳዩት ጽፈው ባኖሩት የግል ማስታወሻቸው ላይ ተመላከተ።

ዛሬ ይፋ በሆነው በዚህ ማስታወሻ ደብተር ሊቀ ጳጳሱ ዲያቢሎስን ሦስት ጊዜ ከማየታቸው በተጨማሪ "የገሃነም ደጆችን" እንደተመለከቱም አስፍርዋል።

ይህን ዲያቢሎስን የተመለከተውን ማስታወሻ ያሰፈሩት እንደ አውሮፓዊያኑ በ2021 ዓመተ ምህረት በዕለተ ማክሰኞ ነው።

ከግል ማስታወሻ ደብተራቸው የተወሰዱ መረጃዎች እንዳመላከቱት ሊቀ ጳጳሱ ዲያቢሎሱን ያዩበትን ሁኔታዎችም ጠቅሰዋል።

ይህም የሆነው አንድ ጊዜ በመኪና፣ ሌላ ጊዜ በቅዳሴ ወቅት በመዘምራን ሰገነት ላይ እንደሆነ አስፍረዋል።

ለሦስተኛ ጊዜ የተመለከቱት ደግሞ ከቫቲካን ኃላፊዎች ጋር ይደረግ በነበረ ስብሰባ መካከል መሆኑ ተጠቅሷል።

ፍራንሲስ ተመለከትኳቸው ካሏቸው ራዕዮች በማስታወስ በተለይም "የዲያቢሎስ የሻካራ ድምፁን ኃይለኛነት መርሳት አልችልም" ሲሉ ጽፈዋል።

ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ይህን የግል ማስታወሻ ያሰፈሩት እንደ አውሮፓዊያኑ ከ1992 እስከ 2024 ዓመተ ምህረት ነበር።

Skip podcast promotion and continue reading
BBC News Amharic የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

በዚህ ማስታወሻ ከጠቀሷቸው ጉዳዮች ሌላው በ2018 ወደ ቺሌ ባደረጉት ጉብኝት መጸጸታቸውን ማመናቸው ነው።

በዚህ ጉብኝት አንድን ወሲባዊ ጥቃት የፈጸመ ቄስን ወንጀል ለመሸፋፈን የሞከረን ሊቀ ጳጳስ ጥፋቱን ተከላክለውለት ነበር። በዚህም ከፍተኛ ትችት ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

እንድ አውሮፓዊያኑ ሚያዝያ፣ 2025 ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከአንድ ቢሊዮን በላይ አማኞች ያሏትን የካቶሊክ ቤተክርስቲንን ለ12 ዓመታት መርተዋል።

ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሦስት ጊዜ ተመልክቼዋለሁ ያሉት ዲዮቢሊስን በተለይ የዐይኖቹ አስፈሪነት ከአእምሯቸው እንዳልጠፋ ገልጸዋል።

"እንደ እሳት ፍም በሚንቀለቀሉ ዐይኖች ተመለከተኝ... ከዚህ ቀደም ከነበረው የበለጠ ኃይለኛ ነበር፤ ዐይኖቹ ልክ ለብላቢ እሳት የመሰሉ ናቸው" ሲሉ ጽፈዋል። ይህ የሆነው ደግሞ በአርጀንቲና የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ ሳሉ በአነስተኛ ፀሎት ቤት ውስጥ እንደነበረ በማስታወሻቸው ላይ አስፍረዋል።

የዲያቢሎስ ጣልቃ ገብተን የተመለከቱት ወደ ቺሌ ባደረጉት ጉብኝት ወቅትና ያን ተከትሎ በነበረው የወሲብ ቅሌት ጉዳይ እንዲሁም ይህን በተመለከተው የሮም ስብሰባ ወቅት እንደነበረም ገልጸዋል።

"ዲያቢሎስን አየሁት ፣ ድምፁን ሰማሁት፤ በድል አድራጊነት ይፎልላል፣ ሁሉንም በእጁ ያስገባ ይመስላል" ሲሉም በግል ማስታወሻቸው ጽፈዋል።

ይሁን እንጂ "ጌታ ራሴን ከእነዚህ ፈተናዎች ሁሉ ነፃ እንድወጣ ዕድል ሰጠኝ፤ ድል ነሳሁት" ሲሉም ጸልይዋል።

ሟቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሰኔ 2018 ምሽት እንደተለመደው ለመተኛት ሲዘጋጁ "የገሃነምን ደጆች" ተገልጠው ማየታቸውንም በዚህ ማስታወሻ ላይ አስፍረዋል።

"መጀመርያ በቁንፅል ተመለከትኩኝ፣ አራደኝ" ብለዋል። ከዚያም ዲያቢሎስ "መቁጠሪያውን እንደ መሳሪያ ወሰደው" ብለዋል።

"ወደ ገሃነም ደጆች መቅረብ አደገኛ ነው፤ ምክንያቱም እሳቱ ሊወጣ እና ሊፋጅ ይችላል" ሲሉም ጽፈዋል።

የቫቲካን ዲካስቴሪ የእምነት አስተምህሮ ኃላፊ እና የፍራንሲስ የልብ ጓደኛ ካርዲናል ቪክቶር ፈርናንዴዝ ይህን የግል ማስታወሻ አርትኦት እንደሠሩ ተነግሯል።

ከአውሮፓውያኑ 1960ዎቹ ጀምሮ የአንድ ሊቃነ ጳጳሳት የግል ማስታወሻ ለሕዝብ ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያው ነው።